የሚስዮናዊነት ስራችን (Missionary Work)

 

ተስፋን መፈንጠቅ በቢሾፍቱ – በኢትዮጵያ የሚገኘው ሕጻናትን የመደገፍ አገልግሎታችን

. . . 2009 – 2018 ድረስ በቢሾፍቱ፣ ኢትዮጵያ በነበረን ተስፋን የመፈንጠቅ አገልግሎት ለ90 ሕጻናት: አልባሳት፣ የሕክምና ወጭዎች እና የትምህርት መገልገያ ቁሳቁሶችን የማሟላት – ያልተቋረጠ፣ የወንጌል መርህን የተከተለ፣ በግልጽነትና ተጠያቂነት የተተገበረ እና አብዛኞቹን ለቁም ነገር ያበቃ እገዛ ተደርጓል።

አሁንም እ. . . 2023 ጀምሮ ይህንኑ የፍቅርና ርኅራኄ (ተስፋን የመፈንጠቅ) አገልግሎታችንን በከተማው ከሚገኘው ሀገር በቀል ማኅበር – ወንጌል ለሁሉም ትውልድ፣ 15 ብርቱ እግዛ የሚያስፈልጋቸው ሕጻናት እና ቤተሰቦቻቸው ድጋፍ እያደረግን እንገኛለን። ድጋፋችን የሚከተሉትን ያካትታል:

–› የትምህርት መገልገያ መሣሪያዎች፣ አልባሳትና ጫማዎችን ማሟላት፣

–› የሕክምና ወጭዎችን (እንደ ሁኔታው) መሸፈን፣

–› በቋሚነት ራሳቸውን የሚያስችል እገዛ – ለአዋቂዎች፣ ማድረግ።

ይህ ድጋፍ ሙሉ ለሙሉ የሚሸፈነው የቤተ ክርስቲየናችን አባላት በሚያደርጉት አስተዋፅዖ/ መዋጮ ነው። በዚህ ረገድ ይህንን አገልግሎት ለማገዝ የሚደረግ የትኛውም ድጋፍ (የገንዘብ ስጦታ) ሕጻናቱን እና ቤተሰቦቻቸውን በዘላቂነት ያግዛል።

ጸሎትዎ፣ ድጋፍዎ እና ማበረታቻዎ፣ እናመሰግናለን፤ እግዚአብሔር ይባርክዎ።

 
 
ስለ እኛ በተጨማሪ
Follow by Email
YouTube