መሠረታዊ እምነት (የእምነት አንቀጽ) (Our Belife)
ቤተ ክርቲያናችን፡
1. መጽሐፍ ቅዱስ
1.1. ስድሳ ስድስቱን መጽሐፍት [የብሉይ ኪዳን (39) እና የዕዲስ ኪዳን (27)] የያዘው መጽሐፍ ቅዱስ ምንም
ስህተት የሌለበት፣ እግዚአብሔር ራሱን ለሰው ልጆች ደህንነት የገለፀበት የማይጨመርበት፣ የማይቀነስበት፣
ብቸኛ እና እውነተኛ የሆነ የመጨረሻ ሥልጣን ያለው መሆኑን፣
1.2. መጽሐፍ ቅዱስ ቅዱሳን ሰዎች በእግዚአብሔር መንፈስ ተመርተው የጻፉት መሆኑን እና የእግዚአብሔር መንፈስ
ያለበት መጽሐፍ መሆኑን (1ኛ ጢሞ 3፣16-17)፣
1.3. መጽሐፍ ቅዱስ ሰው ሁሉ ሊታመንበት የሚገባ፣ ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን መዳን የሚገኝበት መለኮታዊ
እውቀት የሚሰጥ ብቸኛ ቅዱስ መጽሐፍ (2ኛ ጢሞ 3፣15) መሆኑን ታምናላች፡፡
2. እግዚአብሔር
2.1. እግዚአብሔር ያልተፈጠረ፣ ዘላለማዊ እና ሁሉን ቻይ ከሁሉም በላይ የሆነ በምንም የማይመሰለ ሉዓላዊ አምላክ
እንደሆነ (1ኛ ጢሞ 6፣16)፣
2.2. በሰማይና በምድር የሚገኙ ፍጥረታትን ሁሉ የፈጠረ፣ ሁሉን ቻይ፣ ታላቅ፣ ዘላለማዊ፣ ፍጹም የማይለወጥ፣ ራሱን
በሦስት አካል በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ በሚገለጥ በአንድ አምላክ (ዘፍ 1፣1-31፤ ቆሊ 1፣15-16፤ ዘፍ 1፣
26፤ ዘዲ 6፣4-5፤ መዝ 6፣3) ታምናለች፡፡
3. እግዚአብሔር አብ
3.1. እግዚአብሔር አብ ያልተፈጠረ፣ ዘላለማዊ፣ ሁሉን ቻይ፣ ከሁለም በሊይ እንደሆነ (1ኛ ጢሞ 6፣16)፣
3.2. በመፍጠር፣ ፍጥረትን በመጠበቅ፣ ፍጥረትን በማስተዳደርና በመዋጀት፣ በመጨረሻው ፍርድ ያለውን ፍጹም
ሥልጣንና ሉዓላዊነት (ሮሜ 9፣15-16)፣
3.3. የነገሮች ሁሉ ምንጭና መሠረት (ኤፌ 3፣14-15) እንደሆነ ታምናለች፡፡
4. እግዚአብሔር ወልድ
4.1. ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር አብ ዘላለማዊ ልጅ መሆኑን፣
4.2. በመንፈስ ቅዱስ ተፀንሶ ከድንግል ማሪያም መወለዱን (ለቃ 1፣34-35)፣
4.3. በባሕርዩ ፍጹም አምላክና ፍጹም ሰው መሆኑን፣
4.4. ስለ ኃጢአታችን ሞቶ በሦስተኛው ቀን ከሙታን እንደተነሳ፣ በትንሣኤ አካል የተነሳ የትንሣኤው ምሥክር ለሆኑት
ዕርባ ቀናት የታየ መሆኑን፣
4.5. በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ደሙን በማፍሰስ ለኃጢአተኞች ራሱን ቤዛ አድርጎ ሰውን ዋጅቶ ከእግዚአብሔር ጋር
በማስታረቅ ከሞት ተነስቶ በክብር ማረጉን፣ ለሰው ልጅ ሁሉ ሊማልድ ዘወትር በአባቱ ቀኝ በሕይወት መኖሩን፣
4.6. የቤተ ክርስቲያን መሥራችና ራስ መሆኑን፣
4.7. ለፍርድ ዳግም እንደሚመጣም ታምናለች፡፡
5. እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ
5.1. መንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊ ሙላተ አካል ያለው መለኮት መሆኑን፣
5.2. ዕለምን ስለ ኃጢአት፣ ስለ ጽድቅ እና ስለ ፍርድ የሚወቅስ መሆኑን፣
5.3. በአማኞች ውስጥ አድሮ ወደ እውነት ሁለ የሚመራቸው፣ የሚያጽናናቸው፣ የሚያስተምራቸው፣ የቅድስና ኑሮ
ለመኖር እንደሚያስችላቸው፣ ለአገልግሎትም ኀይል እንዯሚሰጣቸው
5.4. የክርስቶስ አካል የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን ለማነጽ የጸጋ ስጦታዎችን ለአማኞች የሚሰጥ መሆኑን ታምናለች፡፡
6. ቤተ ክርስቲያን
6.1. በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመንና በአንድ መንፈስ በመጠመቅ ድግም የተወለዱትን በሙሉ የምትይዝ የክርስቶስ
ሙሽራ መሆኗን፣
6.2. በነቢያትና በሐዋርያት መሠረት ላይ መታነጿን፣
6.3. ክርስቶስ የቤተ ክርስቲያን መሥራችና ራስ፤ እርሷም አካል መሆኗን (ኤፌ 1፣22-23) ታምናለች፡፡
7. ፍርድ
7.1. ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ ወደ ምድር ሲመጣ በሰዎች ሁሉ ላይ እውነተኛ ፍርድ እንደሚያደርግ (ዮሐ 5፣28-
29)፣
7.2. ክርስቶስን አምነው የዳኑ ወደ ተዘጋጀላቸው የዘላለም በረከትና እውነት ሲገቡ በእርሱ ያላመኑ ሰዎች ከሰይጣንና
ከተከታዮቹ ርኩሳን መንፈሳውያን ኃይላት ጋር ወደ ዘላለም ሞት እንደሚጣሉ (2ኛ ተሰ 1፣8-10፤ ራዕ 21፣6-8)
ታምናለች፡፡
8. ቅዱሳን መላእክት
8.1. በእግዚአብሔር ፊት እርሱን የሚያመሌኩና ፈቃዱን የሚያገለግሉ፣ በእርሱም የተፈጠሩና መናፍስት እንደሆኑ
(ዕብ 1፣14)፣
8.2. የእግዚአብሔርን ዕሳብ ለማገለገለ በምድር ለሰዎች ሊገለጡ እንደሚችሉ (ለቃ 1፣27) ታምናለች፡፡
9. ሰይጣን
9.1. በእግዚአብሔር ላይ ያመፀ እና ርኩስ መንፈስ መሆኑን፣
9.2. በመጨረሻው ፍርድ ከተከታዮቹ ጋር ወደ እሳት ባህር እንደሚጣል (ማቴ 25፣41፤ ራዕ 20፣10) ታምናለች፡፡
10. ሰው
10.1. በእግዚአብሔር አምሳል መፈጠሩን፣ በኃጢአት መውደቁንና በዚህም ምክንያት የእግዚብሔር ቁጣ ፍርድ
ያለበት በደለኛ መሆኑን፣
10.2. ሰው መንፈስ፣ ነፍስ እና ሥጋ ያለው በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ፍጡር (1ተሰ 5፥23) መሆኑን
ታምናለች፡፡
11. ውድቀት
11.1. ሰው በተፈጠረ ጊዜ ከኃጢአት ነጻ ሆኖ መፈጠሩን፣
11.2. ሰው በራሱ ስህተት በኃጢአት መውደቁን፣ ከእግዚአብሔር ተለይቶ መጥፋቱን፣ መንፈሳዊ እና ሥጋዊ ሞት
መሞቱን፣ ከሰይጣን ሥልጣን በታች መዋልን ከዚህ የተነሳም ፍጥረት ሁለ ከርግማን በታች መውደቁን
ታምናለች፡፡
12. ደህንነት (ድነት)
12.1. መዳን ስለ ኃጢአታችን ሙሉ ዋጋ ለመክፈል የሞተውንና እኛን ስለማጽዯቅ ከሙታን የተነሳውን ጌታ ኢየሱስ
ክርስቶስን በማመን ብቻ የሚገኝ የጸጋ ስጦታ (ሮሜ 10፣9) መሆኑን፣
12.2. እውነተኛ እምነት ለእግዚአብሔር ፈቃድ እንኖር ዘንድ የአስተሳሰብና የሕይወት ለውጥን በማምጣት
እንደሚገልጥና እንደሚያድግ (1ኛ ተሰ 1፣2-10)፣
12.3. በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነትና ጌትነት ያመነ ሰው ከክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ጋር ኅብረት በማድረግ ጌታ ኢየሱስ
ያዘዘውን የውኃ ጥምቀት መጠመቅ አንደሚኖርበት (ማቴ 28፣18-20፤ ሮሜ 6፣3-4)፣
12.4. በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ የዳነ ሰው በዳግም ምጽዓቱ የደህንነቱን ሙላት እንደሚቀበልና የተለወጠ
የትንሣኤ አካል እንደሚለብስ (ፊሌጵ 3፣20-21፤ 1ኛ ተሰ 4፣14-18) ታምናለች፡፡
13. የክርስቶስ ዳግም ምጽዓት
13.1. ክርስቶስ በእርሱ ያመኑትን ሁለ ወደ እርሱ ለመሰብሰብ ዳግም ወደዚህች ምድር እንደሚመጣ፣
13.2. የብለይና ዕዲስ ኪዳን አማኞች ሁሉ ክርስቶስን ለመቀበል እንደሚነጠቁ እና ከእርሱ ጋር እንደሚኖሩ (1ኛ ቆሮ 15፣20-
21፤ 1ኛ ተሰ 4፣14፤ ራዕ 20፣11-15) ታምናለች፡፡