የቤተ ክርስቲያናችን አመሠራረት እ.ኤ.አ. ከ1989 ዓ.ም. ጀምሮ የተወሰኑ ቅደሳን ወንድሞችና እህቶች በመጽሐፍ
ቅደስ ጥናት በመሠብሠብ የተጀመረ ነው፡፡ በተለያየ ሁኔታ በጀርመን ሀገር ለመኖር ከሀገር ቤት እና ከተለያዩ ሀገሮች
ጌታን የሚያውቁ እና የሚያገለግለ የነበሩ እየበዙ እንዱሁም አዲዱስ ነፍሳትም እየተጨመሩ ኅብረቱ ተጠናከረ፡፡
በመሆኑም በሁለ አቅጣጫ እየሰፋች በቁጥርም እየበዛች በመምጣቷ እ.ኤ.አ ከሐምሌ 27-30/ 1995 ዓ.ም.
የመጀመሪያውን ዓመታዊ ታላቅ ኮንፈራንስ ከመላው የጀርመን ከተሞች ከሚገኙ ኅብረቶች ጋር በመሰባሰብ በግምት
ከ500 በላይ የሚሆኑ ቅደሳንን ተቀብሎ በማስተናገድ በእግዚአብሔር እርዲታ የተሳካ ኮንፈራንስ አድርጋለች።
ከዚህም በኋላ የኅብረቷ የምእመናን ቁጥር መጨመርና የመንፈሳዊ አገልግሎትም እየሰፋ በመምጣቱ ምክንያት በወቅቱ
በነበሩት የኅብረቱ መሪዎች ኅብረቷ በመንግሥት እውቅና እንዱኖራት እ.ኤ.አ. በ1998 ዓ.ም. በጀርመን ሀገር
በኑርንበርግ ከተማ “በኑረንበርግ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን“ በሚል ስያሜ ከኅብረትነት ወደ ቤተ
ክርስቲያንነት ከፍ እንድትልና መንግሥታዊ ሕጋዊነትንም እንድታገኝ ሆናለች። እንዱሁም እ.ኤ.አ. በ2000 ዓ.ም.
የቤተ ክርስቲያን ምሥረታ እና የምስጋና በዓል በማድረግ እና በቀጣይም አገልግሎቷን በተደራጀ መልኩ ስታከናውን
ቆይታ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከደረሰችበት መንፈሳዊም ሆነ የገንዘብ (Financial) አቅም አንጻር ልዩ ልዩ የአገልግሎት
ዘርፎችን በማደራጀት ዱያቆናትን፣ ሽማግሌዎችን እና አንድ ወንጌላዊ በ2010 እንዱሁም ቋሚ በጀት በመመደብ አንድ
የሙለ ጊዜ አገልጋይ የሆነ መጋቢ (ፓስተር) እ.ኤ.አ. በ2006 ዓ.ም. ከሌላ ከተማ አምጥታ በጉባዔ በመጋቢነት
ሾማለች።
አሁን የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕጋዊ ስያሜ “የጸጋው ቃል አማኞች ቤተ ክርስቲያን በኑርንበርግ” በመባል በኑርንበርግ
ከተማ እንዱሁም “የጸጋው ቃል አማኞች ቤተ ክርስቲያን በቩርዝቡርግ” በቩርዝቡርግ ከተማ ሁለተኛ አጥቢያ
በመትከል ቅደሳንን ታገለግላለች፡፡ በተጨማሪ በታላቁ ተልዕኮ አገልግሎትም ወደ ብዙዎች ወንጌል እያደረሰች
የምትገኝ ቤተ እምነት ሆናለች፡፡ የቤተ ክርስቲያናችን አገልግሎቶች በብዝሃ ቋንቋ (አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ትግርኛ
እና ጀርመንኛ) ለብዙዎች ተደራሽ ሲሆን በማኅበራዊ ሚዲያም የእግዚአብሔርን መልእክት ለሰው ልጆች
ታደርሳለች፡፡