ጸሎት፡
ምንም ነገር ከማድረጋችን በፊት የእግዚብሔርን ፊት በጸሎት በመፈለግ ምሪትን መቀበል፣
ወንጌል ሥርጭት፡
በምድር ላይ የምንኖርበት ዋና ዓላማ ታላቁ ተልዕኮ እንደመሆኑ መጠን ባገኘነው አጋጣሚ ሁለ በግልና በጋራ የምሥራቹን ማሰራጨት፣
ትምህርት፡
የሁለ ነገር መሠረቱ የእግዚአብሔር ቃል እውነት በመሆኑ አማኞችን በተለያዩ ደረጃዎች ማስተማር፣
ግልጽነት፡
ማንኛውም የቤተ ክርስቲያኒቱ አሠራር፣ ወጭና ገቢ እና ንብረት አስተዳደር ለአባላት ግልጽ በሆነ አሠራር እንዲሆን ይደረጋል፣
ታማኝነት፡
ለእግዚአብሔርና ለእግዚአብሔር ሕዝብ በጊዜ፣ በአገልግሎትና በገንዘብ ታማኝ በመሆን በምሳሌነት መመላለስ፣
ተጠያቂነት፡
በእግዚአብሔርም ሆነ በሕዝቡ ፊት ተጠያቂዎች እንደመሆናችን መጠን በነገር ሁለ ምሳሌ በመሆን በቃልና በሥራ በምናደርገው ነገር ሁለ መጠንቀቅ፣
አገልጋይነት፡
የእግዚአብሔርን ሕዝብ ዝቅ ብለን በባለ አደራነትና በአገልጋይነት መንፈስ ማገልገል፣
መንፈሳዊ አንድነትን መጠበቅ፡
የኅብረቱን መንፈሳዊ አንድነት ለመጠበቅ ትጋት ማድረግ፣ በፍቅርና በአክብሮት መመላለስ፣ ለመሪዎች በእኩል መታዘዝ፣ እውነትን በፍቅር መግለጽ፣
ቤተሰባዊነት፡
በፍቅር፣ በመከባበር፣ በመተሳሰብ እንደ ቤተሰብ በወንድማማችነት/ እህትማማችነት መኖር፣
ምሥጢር ጠባቂነት፡
በአገልግሎት አጋጣሚ የሚገኙ ማናቸውንም ለሌሎች መገለጽ የሌለባቸውን ነገሮች በምሥጢር መጠበቅ፡፡