ሰው ሁሉ ኃጢአትን ሰርቷል፣ የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎታል፡፡ ስልሆነም ክብር ለጎደለው ለዚህ ፍጥረት
ወንጌልን መስበክ፣
ዕለምና ኃጢአትን ክደው ራሳቸውን ለክርስቶስ ሕያውና ቅዱስ መስዋዕት አድርገው የሚያቀርቡ ደቀ መዛሙርትን
ማፍራት፣
አማኞች ጥሪያቸውንና የተሰጣቸውን የጸጋ ስጦታ እንዲያውቁ በማስተማር፣ ቃልን በማስታጠቅና በማነሳሳት በሁሉ
የሕይወት አቅጣጫ ለእግዚአብሔር የተሰጡ እንዲሆኑ በማስተማር ተተኪዎችን ማፍራት፣
በእውነትና በመንፈስ እግዚአብሔርን በማምለክ አማኞችን በእውነተኛ አምልኮ በግልና በጋራ ከእግዚአብሔር ጋር
እውነተኛ ኅብረት እንዲያደርጉ መርዳትና ማበረታታት፣
እውነተኛ የመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ እንዲቀጣጠል በጸሎትና በእግዚአብሔር ቃል ማስተማር፣
ሰውን ሁለ በሁለንተናዊ መልኩ በበጎ ሥራ፣ በፍቅርና በርኅራኄ፡ ዘርን፣ ፆታን እና/ ወይም ቀለምን ሳንለይ በጸጋ፣
በእውቀት፣ በጉልበት፣ በገንዘብ እስከ ጌታ ምጽዓት ድረስ በታማኝነትና በትጋት ማገልገል፣
ሚስዮናዊ አገልግሎቶችን መፈፀም፤ ስለ ሚስዮናዊ አገልግሎት ከሌሎች ጋር መተባበር፡፡